+251-993-818276 akofeda@gmail.com Addis Ababa, Ethiopia

ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ የፓትሪያርኩ መልዕክት

በተዋረድ ያላችሁ ወንድሞቼ እና በጌታ የተወደዳችሁ ልጆቼ

የታላላቅ ከተሞች እምብርት ከሆነችው ከተማ፣ የታላቋ ቤተክርስቲያን የሃጊያ ሶፍያ**** መገኛ ከሆነችው ከተማ፣ በዓለም ላይ ቀድሞ ባማይታወቅ መልኩ እንደ ሰው ልጆች የገጠመንን መከራ እና  የተከሰተውን ኮቪድ-19 ኝ ወረርሽኝን በማስመልከት ለሴቶችም፣ ለወንዶችም፣ ለልጆችም ይህን መልእክቴን ለማስተላለፍ ወደድኩ

የእናት ቤተክርስቲያን ድምጽ በእንዲህ ዓይነቱ ሠዓት ዝም አይልም፡፡ በዘመናት ከትውፊት እና ከሥርዓተ ቅዳሴው በተማርነው እና ባወቅነው መሰረት በማበረታታት እና በማስተዛዘን እንዲህ እንናገራለን፡፡

እራሳቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን በመተው እና በመስዋዕትነት የሚታገሉትን በመጥቀስ በታላቅ አክብሮት ልናመሰግናቸው እንወዳለን፡፡ በተለይም፡-

  • በሕመሙ የተያዙትን እና እነርሱን በመርዳት ላይ ያሉትን የሕክምና ባለሙያዎችን ዶክተሮችን እና ነርሶችን
  • ከበሽታው እና ከጭንቀቱ እንገላገል ዘንድ ለበሽታው መድኃኒት ለማግኘት ለሚተጉ ተመራማሪዎች እና ሳይንቲስቶች
  • እና ለሌሎች ይህንን ወረርሽኝ እየታገላችሁ ላላችሁ በሙሉ ታላቅ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ

እያደረጋችሁት ያለው ነገር፤ ለሁሉም ማኅበረሰብ የቀረበ እጅግ የከበረ ስጦታ ሲሆን ታላቅ እና የከበረ ምስጋና የሚገባው መስዋዕትነትም ጭምር ነው፡፡ በመሆኑም ሁላችንም በአንድነት እና በኅብረት እናመሰግናችኋለን፣ እናከብራችኋለን፡፡ ይህም የሚሆነው ከመጋረጃ ጀርባ ሳይሆን በሁሉም ቦታና ጊዜ ነው፡፡ ሐሳባችንም ፀሎታችንም ከእናንተ ጋር ነው፡፡

በዚህ የትግል ወቅት፡- ይህን አስጊ ሁኔታ ለማለፍ የሚስፈልገውን ዕቅድ ማውጣትና መጋፈጥ በቅድሚ የሚመለከታቸው የተመረጠው መንግስታችን፣ መንግስታት፣ እና የሚመለከታቸው የጤና ኃላፊዎች ሲሆኑ እነዚህን በሰው ልጆች ሁሉ ላይ በጠላትነት የተነሳውን፣ የማይታየውን ነገር ግን በአሁን ሰዓት የሚታወቀውን ጠላት የሚዋጉ የጦር አዛዦቻችን እንላቸዋለን፡፡

በጫንቃቸው ላይ ያለው ኃላፊነት የሁላችንንም ትብብር ይሻል፡፡ በግልም በማህበርም ኃላፊነታችንን ልንወጣ የሚገባበት ሠዓት አሁን ነው፡፡

ስለዚህ ወንድሞች ሆይ፡ መንግስታችን እና የጤና ኃላፊዎቻችን የሚነግሩንን አስቸጋሪ ግን አስፈላጊ ነገሮች በታማኝነት እንፈጽም ዘንድ እኛ መንፈሳዊ አባቶቻችሁ እንማለላችኋለን፡፡ የሚነገረን ሁሉ የዚህን ቫይረስ ስርጭት ለመግታት ይቻል ዘንድ ስለ እኛው ደህንነት እና መልካምነት ስለሆነ፣ ከዚህ ነገር የምንገላገለው ሙሉ በሙሉ በምናደርገው ትብብር መሆኑን አንዘንጋ፡፡

ምናልባት አንዳንዶቻችሁ ይህ በመንግስት የሚወጣ አዋጅ፣ ዕምነታችንን የሚጎዳ እና የሚያኮስስ ነው የሚል ስሜት ሊያድርባችሁ ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ጉዳዩ ስለ እምነታችን ሳይሆን ስለ አማኞቻችን ነው፡፡ ስለ ክርስቶስ ሳይሆን ስለ ክርስቲያኖቻችን ነው፡፡ ሰው ስለሆነው አምላክ ሳይሆን ስለ ሰዎች ነው፡፡

ሃይማኖታችን ባህላችን ላይ መሰረት ያደረገ ሕያው ሃይማኖት ስለሆነ ምንም ዓይነት ነገር ሊወስነው እና ሊጫነው አይችልም፡፡ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ሊወሰን እና ሊገታ የሚገባው ነገር የሕዝቦች መሰባሰብ እና ትልልቅ ጉባኤ ነው፡፡  በቤታችን በመቀመጥ በዙሪያችን ያሉትን እንጠብቃቸው፡፡ በቤታችን በመሆን በመንፈሳዊ አንድነታችን እያንዳንዳችን ለሰው ዘር በሙሉ ፀሎት እናድርግ፡፡

ወደ ተስፋይቱ ምድር በበረሃ እንደሚደረግ ጉዞ ይህንን ዘመን እናልፈዋለን፡፡ ወንድሞቻችንም በእግዚአብሔር ረድዔትና ዕገዛ መድኃኒቱን ያገኙታል፡፡

በጸሎታችን ኃይልና በሳይንስ እገዛ እንደምናሸንፍ እርግጠኞች ነን፡፡ ስለዚህ የንሰሃ እና የቅድስና ተጋድሎዋችንን እየፈጸምን በመንፈስ አንድ እንሆን ዘንድ ይገባል፡፡

ጎረቤቶቻችን በበሽታው ሲማቅቁ እየተመለከትን ጥቂቶችም በሞት ተነጥቀው ከመካከላችን ሲለዩን እያየን ነው፡፡  ቅድስት ቤተክርስቲያችን ለታመሙት ፈውስን፣ በሞት ለተለዩን ምህረትን እና የችግሩ ሰለባ ለሆኑ ቤተሰቦችም ጥንካሬን እና መጽናናትን ያገኙ ዘንድ ተስፋ በማድረግ ጸሎት ታደርጋለች፡፡

ደመናው ተገፎ፣ የቅድስና ፀሐይም የዚህን መርዛማ ቫይረስ ችግር አስወግዶ መከራው ያልፋል፡፡ ነገር ግን ሕይወታችን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተቀይሮ ያልፋል፡፡ ይህ ፈተና ፍቅርና አንድነትን የምንመሰርትበትን የዕድል አቅጣጫ አመላክቶናልና፡፡

ውድ በጌታ የተወደዳችሁ ልጆቼ ሆይ፣ የእግዚአብሔር ጸጋ፣ የቅድስተ ቅዱሳን ወላዲተ-አምላክ አማላጅነት፣ መንገዳችንን ያቅናልን፡፡ በቤታችን ያደረግነውን መለየት ወደ እውነተኛ አንድነት ይቀይርልን፡፡ ወደ እውነተኛው እና እግዚአብሔርን ወደ ሚያስደስተው ይመልሰን፡፡ ጸሎታችንም መዳረሻችንም ይሁን፡፡ አሜን፡፡

እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡ ብርታት ይኑራችሁ፡፡

የቁስጥንጥንያው ፓትሪያክ ብጹዕ በርቶሎሜዎስ ቀደማዊ ኮሮና ቫይረስን አስመልክተው በመጋቢት 10/2012 /March 19-20/ያስተላለፉ መልዕክት

*** ሃጊያ ሶፍያ በቱርከ እስታንቡል ውስጥ የምትገኝ ለ1000 ዓመታት ያህል በዓለማችን ትልቋ ካቴድራል በመባል የምትታወቅ ቤተክርስቲያን ነች፡፡ ባለ ትልቅ ጉልላት ቤተክርስቲያን በመሆኗም የሕንጻ ዲዛይነሮችን ታሪክ የቀየረችም ነች፡፡ ይሁን እንጂ በኋላ በ1453፣ በኦቶማን ቱርክ ሙስሊሞች አማካይነት ወደ መስኪድነት ተቀይራ ለተመልካች ዝግ ሆና ስትኖር የነበረች ሲሆን ዛሬ ከ 1931 ጀምሮ በሙዚየምነት የምታገለግል ብዙ ተመልካች ያላት ቦታ ነች፡፡

Please follow and like us:
error0
fb-share-icon20

1 thought on “ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ የፓትሪያርኩ መልዕክት”

  1. admin says:

    ምናልባት አንዳንዶቻችሁ ይህ በመንግስት የሚወጣ አዋጅ፣ ዕምነታችንን የሚጎዳ እና የሚያኮስስ ነው የሚል ስሜት ሊያድርባችሁ ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ጉዳዩ ስለ እምነታችን ሳይሆን ስለ አማኞቻችን ነው፡፡ ስለ ክርስቶስ ሳይሆን ስለ ክርስቲያኖቻችን ነው፡፡ ሰው ስለሆነው አምላክ ሳይሆን ስለ ሰዎች ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Post

በ 325 በኒቂያ ጉባኤ የተደረጉ ቀኖናዊ ዉሳኔዎች

በአርዮስ የምንፍቅና ትምህርት ምክንያት በ325 ዓ.ም በንጉስ ቆስጠንጢኖስ ዘመን ቤተክርስቲያን የመጀመሪያወን ዓለም ዐቀፍ ጉባኤ 318 ብጹዐን አበው በተሰበሰቡበት አደረገች፡፡ አርዮስን ከማውገዝ እና የእግዚአብሔር ልጅ ወልድ በባህርይ ከአብ ጋር አንድ መሆኑን

ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘኑሲስ

ሕይወቱ የቅዱስ ባስልዮስ ታናሽ ወንድም ቅ. ጎርጎሬዎስ በ335 ዓ.ም ተወለደ፡፡ የልጅነት ሕይወቱ ብዙ አይታወቅም፡፡ በቂሳርያ እቤት ውስጥ መንፈሳዊ ትምህርትን እንደተማረ ይገመታል፡፡ እሱም በአንድ ቦታ ላይ ከሐዋርያ በኋላ የተነሳ የነሱ አቻ

የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና የመንግስት ባለስልጣናት ግንኙነት

በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከስነ ምግባር ጉድለት እና ከእምነት ጋር በተያያዘ ለረዥም ጊዜ ከባለስልጣናት ጋር ሲታገል ኖሯል፡፡ ከመንግስት ጋር መሞዳመድ የሚባል ነገርንም አያውቅም፡፡ በተለይ በቁስጥንጥንያ እያለ አብዝቶ ስለነዚህ