+251-993-818276 akofeda@gmail.com Addis Ababa, Ethiopia

ዘመነ ጾም

የብልጽግናን እና የጣፋጭ ምግብን ጣዕም አትልመድ

ምግብህ ቀለል ያለ እና የተመጠነ ይሁን

መጽሐፍ ‹‹በሆድህ ጥጋብ አትሳሳት›› ይላልና (ምሳ 24፡15)

ቴዎድሮስ ባሕታዊ

ዘመነ ጾም

ዘመነ ጾም የሚባለው በኢየዓርግና በኢይወርድ የተወሰነ ሆኖ እናገኘዋለን፣ ይኸውም ዓቢይ ጾም የካቲት 1 ቀን ቢገባ ማለቂያው መጋቢት 25 ቀን ሆኖ መጋቢት 26 ቀን ፋሲካ ይሆናል፣ የጾሙ ዕለታት ቁጥር 55 ዕለታት ነው፡፡ ከዚህ ሌላ ጾም መጋቢት  ቀን ቢገባ ማለቂያው ሚያዝያ 29 ቀን ሆኖ ትንሣኤ ወይም ፋሲካ ሚያዝያ 30 ቀን ይወላል፣ የጾሙ ዕለታት ቁጥርም 55 ይሆናል፡፡ ከዚህ አይበልጥም ከዚህ አይወርድም፡፡

ጆሮ ይጹም፣ ዐይን ይጹም፣ አፍ ይጹም
ጆሮ ይጹም፣ ዐይን ይጹም፣ አፍ ይጹም

ጾም፤ ጦመ፤ እህል ውሃ ሳይቀምስ ዋለ፤ ከሥጋ ከቅቤ ተከለከለ

ጦመኛ(ኞች)፤ ባለጦም፤ ጦም ወዳድ ጧሚ፤ ውሎ የሚበላ ሥጋና ቅቤ የማይቀምስ

ተረት፤ ሰይጣን ጦመኛ ሲሆን ዘላለም ሰይጣን ነው፡፡

ጦም የሚባሉ 7 ናቸው፡-

  • የሐዋርያት ጦም
  • ዐርብ እና ሮብ
  • የፍልሰታ ጦም
  • የነቢያት ጦም
  • የልደትና የጥምቀት ገሃድ
  • የነነዌ ጦም
  • የሁዳዴ ጦም ናቸው


ጾም በብሉይ ኪዳን

በብሉይ ኪዳን ጾም ከፍተኛ ቦታ አለው፡፡ የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከእግዚአብሔር ጋር በሚገናኙበት ወራት እህልና ውሃ በአፋቸው አይገባም ነበር (ዘጸ 34፡28)፡፡ በኃጢአት ብዛት የታዘዘው የእግዚአብሔር መዓት የሚመለሰው ሕዘቡ በጾም ሲለምኑትና ሲማልዱት ነበር (ዮናስ 2፡7፤ አስ 4፡ 15-16)፡፡

ጾም በአዲስ ኪዳን

በሐዲስ ኪዳንም ጾም ሰው ሰራሽ ሕግ ሳይሆን እራሱ ክርስቶስ የስራ መጀመሪያ አድርጎ የሰራው ሕግ ነው (ማቴ 4፡2፤ ሉቃ 4፡2)፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን በቁራኝነት አብሮ የሚኖር መንፈስ ርኩስ ሰይጣን እንኳ በጾም የሚወገድ መሆኑን መድኃኒታችን ተናግሮአል (ማቴ 17፡21፤ ማር 9፡2)፡፡ በቤተክርስቲያን የታዘዙ ሐዋርያትም በየጊዜው ከመንፈስ ቅዱስ ትዕዛዝ የሚቀበሉት በጾም  አና በጸሎት ላይ እንዳሉ ነበር (ሥራ 12፡2)፡፡ ለስብከተ ወንጌል የሚያገለግሉ ዲያቆናትና ቀሳውስትም የሚሾሙት በጾምና በጸሎት ነበር (ሥራ 13፡3፤ 14፡23)፡፡እነ ቆርኖሌዎስ ያላሰቡትን ያዩና ያገኙ በጾምና በጸሎት ፈጣሪያቸውን ማልደው ነው፡፡ (ሥራ 10፡30)

በጾም የሚከለከሉ ነገሮች
በጾም ወራት ላምሮት ለቅንጦት የሚበሉ፣ ወይም ለመንፈሳዊ ኃይል ተቃራኒ የሆኑ ሥጋዊ ፍትወትን የሚያበረታቱ፣ ሥጋንና የሚያሰክሩ መጠጦችን (ዳን 10፡2-3)፣ ቅቤና ወተትን (መዝ 108፡24) መከልከል ታዟል፡፡ በተጨማሪም ባልና ሚስት በጾም ወራት በአልጋ አይገናኙም (1ቆሮ 7፡5፤ 2ቆሮ 6፡6)፡፡  በጾም ወራት ከመባልዕት (ከሚበሉ ነገሮች) መከልከል ብቻ ሳይሆን ዐይን ክፉ ከማየት፣ አንደበት ክፉ ከመናገር፣ ጆሮ ክፉ ከመስማት መቆጠብ እንደሚገባ ተጽፎአል፡፡ ‹‹ይጹም ዐይን፣ ይጹም ልሳን፣ እዝንኒ ይጹም እምሰሚዐ ኅሱም በተፋቅሮ›› ድጓ ዘቅዱስ ያሬድ

ምንጭ፡ መዝሙረ ማኅሌት ወቅዳሴ (ገጽ 100-101)፤ በሊቁ አፈወርቅ ተክሌ (የቅኔ መምህር)

ማስታወሻ፡ ሊቁ አፈወርቅ የቅኔ መምህር ብቻ ሳይሆኑ የመጻሕፍት መምህር ጭምርም ናቸው፡፡ ባጠቃላይ ይህ ቀረሽ የማይባሉ በዘመናችን በማናቸውም የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ላይ ተጠያቂ ሊቅ ናቸው፡፡ ከላይ የተጠቀሰቸው መጽሐፋቸው፣ የዓመቱን መዝሙራት በወር በመከፋፈል የየወራቱን ጸባይ፣ ስያሜ፣ በየወራቱ የሚውሉትን በዓላት፣ ባህላዊ እና ትውፊታዊ ስርዓቶችን ከተረቶች ጋር በማዋዛት የሰንበታቱን እና የቤተክርስቲያንን ታላላቅ በዓላት የምትናገር በይዘቷ የቀደሙ የቤተክርስቲያን ሊቃውንት የሚጽፉት ዓይነት ጠንካራ መልእክት ያላት መጽሐፍ ስለሆነች አንባቢያን በእያንዳንዳችን ቤት ብትኖረን ብዙ የምንማርባት መሆኗን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

Please follow and like us:
error0
fb-share-icon20

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Post

ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ የፓትሪያርኩ መልዕክት

በተዋረድ ያላችሁ ወንድሞቼ እና በጌታ የተወደዳችሁ ልጆቼ የታላላቅ ከተሞች እምብርት ከሆነችው ከተማ፣ የታላቋ ቤተክርስቲያን የሃጊያ ሶፍያ**** መገኛ ከሆነችው ከተማ፣ በዓለም ላይ ቀድሞ ባማይታወቅ መልኩ እንደ ሰው ልጆች የገጠመንን መከራ እና

መድኃኔዓለም ክርስቶስ

በቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ምንጭ፡ The Fathers of the Church Patristic Series 91 ለሟች ሁሉ የሕይወት ምንጭ ይሆን ዘንድ የሟች አዳምን ሥጋ ለለበስክ ለአንተ ክብር ይገባሃል፡፡ አንተ፤ ብዙ ፍሬ አፍርታ እንድትበቅል፣

ሞትን በሞት የሻረ

በቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊምንጭ፡ The Fathers of the Church Patristic Series 91 ጌታችን በሞት ላይ ተረማመደ፡፡ ከሞት ባሻገር ላለ መንገድም መረማመጃን አዘጋጀ፡፡ በሞት መንገድ ሞትን ያለፈቃዱ ያስወግደው ዘንድ በፈቃዱ ለሞት የተገዛ