+251-993-818276 akofeda@gmail.com Addis Ababa, Ethiopia

ሲዖልን መሸጋገሪያ

ሁሉን ከምትሰለቅጠው ሲዖል በመስቀሉ ሰውን ወደ ሕይወት ያወጣው የጥበበኛው አናጺ ልጅ እነሆ፡፡ በዛፍ ምክንያት ወደ ሲዖል የወረደው የሰው ልጅ በዛፍ ምክንያት ወደ ሕይወት ተሻገረ፡፡ ከፍጥረቱ ጋር ተቃርኖ እንደሌለው እናውቅ ዘንድ መራራነትን ከቀመስንባት ዛፍ ጥፍጥናንም ቀመስን፡፡ ነፍሳት ከሲዖል ወጥተው ወደ ሕይወት ይሻገሩ ዘንድ መስቀልህን በሞት ላይ ለሰቀልክልን ለአንተ ክብር ምስጋና ይድረስህ፡፡

Holy Cross

አማንያንም፣ ኢኣማንያንም የተሰናከሉበትን የጣዖት አምልኮ በመስቀልክ ላስወገድክ ላንተ ክብር ይገባሃል፡፡ ሕይወት መስሏቸው ወደ አዘቅት የወረዱትን፣ ወደ እውነተኛው ሕይወት ለመለስክ፣ የሕይወት መድሐኒት ለሆንከው ለአንተ ምስጋና ይገባሃል፡፡ ጠፍተው የተገኙቱ ያመሰግኑሃል፤ የጠፉትን በማግኘትህም፣ ያልጠፉት እና ሁሌም የሚኖሩቱን መላዕክት ደስ አሰኘሃቸው፡፡ በሰላምህ በመካከል የነበረውን ጠላትነት አስወግደህላቸዋልና ያልተገዘሩቱ ያመሰግኑሃል፡፡ ውጭያዊ ምልክት የሆነውን እና ያንተ የሆኑት ያንተ ለመሆናቸው የሚለዩበትን ግዝረት በሥጋህ ተቀብልክ፡፡ የተገዘሩቱ በመገዘራቸው ብቻ ያንተ እንዳልሆኑ ይታወቅ ዘንድ የልብ መገዘርን ምልክት አድርገህ ሰጠኸን፡፡ ያንተ ወደ ሆኑት መጣህ፣ እነርሱ ግን አልተቀበሉህም (ዮሐ 1፡11)፣ ያአንተ ያልሆኑቱ ግን ከልጆች የተረፈውን ፍርፋሪ ታበላቸው ዘንድ በኋላህ ያለቅሳሉ፡፡

በቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ

ምንጭ፡ The Fathers of the Church Patristic Series 91

Please follow and like us:
error0
fb-share-icon20

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Post

ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘኑሲስ

ሕይወቱ የቅዱስ ባስልዮስ ታናሽ ወንድም ቅ. ጎርጎሬዎስ በ335 ዓ.ም ተወለደ፡፡ የልጅነት ሕይወቱ ብዙ አይታወቅም፡፡ በቂሳርያ እቤት ውስጥ መንፈሳዊ ትምህርትን እንደተማረ ይገመታል፡፡ እሱም በአንድ ቦታ ላይ ከሐዋርያ በኋላ የተነሳ የነሱ አቻ

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ

የ፳፻፲፭ ዐቢይ ጾምን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት መልእክት! • በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ምእመናት እንዲሁም ኢትዮጵውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ! እንደ ስሑትና ደካማ ሰብአዊ ባሕርያችን ሳይሆን

አርዮሳውያንን አልቀበልም በማለቱ በመንግስት ዛቻ የደረሰበት ቅዱስ አባት

ቅዱስ ባስሊዮስ በ329 ተወልዶ በ379 በ50 ዓመቱ ከዚህ ዐመት እንግልት በእረፍት ተለየ፡፡ ቅዱስ ባስልዮስ በዐለማዊ ትምህርቱ ከቅዱሳን አባቶቹ ሁሉ ቀዳሚውን ቦታ የሚይዝ ሲሆን በመንፈሳዊ ሕይወቱ እና እውቀቱም የመነኩሴ ሊቅ እና