+251-993-818276 akofeda@gmail.com Addis Ababa, Ethiopia

በ 325 በኒቂያ ጉባኤ የተደረጉ ቀኖናዊ ዉሳኔዎች

በአርዮስ የምንፍቅና ትምህርት ምክንያት በ325 ዓ.ም በንጉስ ቆስጠንጢኖስ ዘመን ቤተክርስቲያን የመጀመሪያወን ዓለም ዐቀፍ ጉባኤ 318 ብጹዐን አበው በተሰበሰቡበት አደረገች፡፡ አርዮስን ከማውገዝ እና የእግዚአብሔር ልጅ ወልድ በባህርይ ከአብ ጋር አንድ መሆኑን በውሳኔ ከማጽናት ባሻገር 20 ቀኖናዊ ውሳኔዎችን አሳልፋለች፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ወቅታዊ ጉዳይ የሆኑትን እና ሌሎችን ተርጉመን አሰቀምጠናል፡፡

  1. በገዛ ፈቃዱ ራሱን ጃንደረባ ያደረገ ማንም ቢሆን ከክህነት አገልግሎት ይከልከል፡፡ ነገር ግን በአረመኔዎች ወይም በጌታው ወይም በህመም ምክንያት በቀዶ ጥገና ጃንደረባ ከሆነ በአገልግሎቱ ይቆይ
  2. በአሰገዳጅ ነገሮች መፈጠር ወይም በግለሰቦች ጥድፊያ ምክንያት ብዙ ነገሮች ያለ ቤተክርስቲያን ስርዓት እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ ይሁን እንጂ ማንም አዲስ አማኝ ወይም በቂ ልምድ የሌለው ሰው በኤጲስ ቆጶስነት አይሾም፡፡ ከመሾሙ በፊትም ሆነ በኋላ በዝሙት ኃጢአት መውደቁ ቢታወቅ ከሹመቱ ይታገድ፡፡
  3. ቅዱስ ሲኖዶስ (የኒቂያው ጉባኤን ማለት ነው) ማንም ኤጲስ ቆጶስ፣ ካህን ወይም ዲያቆን ከእናቱ፣ ከእህቱ፣ ወይም ከአክስቱ ወይም ጥርጣሬ ላይ ሊጥለው ከማይችለው ሰው ውጭ በቤቱ ከሌላ ሴት ጋር አይኑር፡፡
  4. አንድ ኤጲስ ቆጶስ ሲሾም የሀገሩ ጳጳሳት በሙሉ ባሉበት ይሾም፡፡ ይሁን እንጂ አጣዳፊ በሆነ ምክንያት ወይም ከቦታ ርቀት የተነሳ ይህን ማድረግ ባይቻል፤ መገኘት ያልቻሉ ሌሎች ጳጳሳት ፈቃደኝነታቸውን በጽሑፍ ያሳውቁ፡፡ ከዛም ቢያንስ ሦስት ጳጳሳት ሆነው በአንድነት ሹመቱን ያከናውኑ፡፡ በየትም ቦታ የሚደረገው ሹመት ግን የሚጸድቀው ሊቀ-ጳጳሱ (ፓትርያርኩ) ሲያጸድቀው ብቻ ነው፡፡ (It is by all means proper that a bishop should be appointed by all the bishops in the province; but should this be difficult, either on account of urgent necessity or because of distance, three at least should meet together, and the suffrages of the absent [bishops] also being given and communicated in writing, then the ordination should take place. But in every province the ratification of what is done should be left to the Metropolitan.) ይኸው አባባል ከ 75 አመት በፊት በሲፕርያን ተገልጾ ይገኛል፡፡(Epistles of Cyprian 67)
  5. በዓመት ሁለት ጊዜ ጠቅላላ ጉባኤ (ሁሉም ጳጳሳት የሚገኙበት የሲኖዶስ ስብሰባ) ይደረግ፡፡ አንዱ ከዐቢይ ጾም በፊት፡፡ ሌለኛው ከዐቢይ ጾም በኋላ፡፡ በአንድ ሀገረ ስብከት ጳጳስ የተወገዘን ካህን ወይም ምዕመን በሌላ ሀገረ ስብከት ጳጳስ አይፈታ፡፡ ነገር ግን በተንኮል፣ በጸብ ወይም ደግነት በማጣት የተከናወነ ውግዘት ከሆነ ከሁሉም ሀገረ ስብከት ጳጳሳት በሚሰበባሰቡበት ሲኖዶስ በጥንቃቄ ተመርምሮ ጉዳዩ ይታይ፡፡ ሁሉም ጳጳሳት ባሉበት ጳጳሳቸው ላይ በደል ያደረሱ ሰዎች ተገቢው ፍርድ ይሰጣቸው፡፡
  6. ማንም በሰንበት ወይም በበዓለ ሃምሳ እየሰገደ ጸሎት አያድርስ፡፡ ሁሉም ጋር ወጥ የሆነ ስርዓት ይኖር ዘንድ በሁሉም ሀገረ-ስብከት በነዚህ ቀናት ጸሎት ተቁሞ ይደረግ፡፡
  7. ከሀገረ ስብከቱ ፈሪሃ እግዚአብሔር ስለሌለው ወይም በግዴለሽነቱ የተባረረን ሌላ ሀገረ ስብከት አይቀበለው፡፡ ማንኛውም ተገቢው ገደብ ይጣልበት፡፡ ወደ ሀገረ ስብከቱም እንዲመለስ ይደረግ፡፡ አልመለስ ሚል ከሆነ ግን ይወገዝ፡፡ ይሁን እንጂ ከነበረበት ሀገረ ስብከት ሊቀ-ጳጳስ ውጭ ሹመት ቢሰጠው፡፡ ሹመቱ ተቀባይነት አይኑረው፡፡
  8. በረብሻ እና ባለመረጋጋት ምክንያት ጳጳሳት፣ ካህናትና ዲያቆናት ካለ ሀገረ ስብከታቸው ሲሰሩ ይታያል፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በኋላ ይህ ድርጊት ተቀባይነት ስለሌለው ወደ ቀደመ ሀገረ ስብከታቸው ይመለሱ፡፡

ይቆየን

ኮፌዳ

Please follow and like us:
error0
fb-share-icon20

1 thought on “በ 325 በኒቂያ ጉባኤ የተደረጉ ቀኖናዊ ዉሳኔዎች”

  1. admin says:

    አንድ ኤጲስ ቆጶስ ሲሾም የሀገሩ ጳጳሳት በሙሉ ባሉበት ይሾም፡፡ ይሁን እንጂ አጣዳፊ በሆነ ምክንያት ወይም ከቦታ ርቀት የተነሳ ይህን ማድረግ ባይቻል፤ መገኘት ያልቻሉ ሌሎች ጳጳሳት ፈቃደኝነታቸውን በጽሑፍ ያሳውቁ፡፡ ከዛም ቢያንስ ሦስት ጳጳሳት ሆነው በአንድነት ሹመቱን ያከናውኑ፡፡ በየትም ቦታ የሚደረገው ሹመት ግን የሚጸድቀው ሊቀ-ጳጳሱ (ፓትርያርኩ) ሲያጸድቀው ብቻ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Post

ሞትን በሞት የሻረ

በቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊምንጭ፡ The Fathers of the Church Patristic Series 91 ጌታችን በሞት ላይ ተረማመደ፡፡ ከሞት ባሻገር ላለ መንገድም መረማመጃን አዘጋጀ፡፡ በሞት መንገድ ሞትን ያለፈቃዱ ያስወግደው ዘንድ በፈቃዱ ለሞት የተገዛ

ዘመነ ጾም

የብልጽግናን እና የጣፋጭ ምግብን ጣዕም አትልመድ ምግብህ ቀለል ያለ እና የተመጠነ ይሁን መጽሐፍ ‹‹በሆድህ ጥጋብ አትሳሳት›› ይላልና (ምሳ 24፡15) ቴዎድሮስ ባሕታዊ ዘመነ ጾም ዘመነ ጾም የሚባለው በኢየዓርግና በኢይወርድ የተወሰነ ሆኖ

መድኃኔዓለም ክርስቶስ

በቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ምንጭ፡ The Fathers of the Church Patristic Series 91 ለሟች ሁሉ የሕይወት ምንጭ ይሆን ዘንድ የሟች አዳምን ሥጋ ለለበስክ ለአንተ ክብር ይገባሃል፡፡ አንተ፤ ብዙ ፍሬ አፍርታ እንድትበቅል፣