+251-993-818276 akofeda@gmail.com Addis Ababa, Ethiopia

የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና የመንግስት ባለስልጣናት ግንኙነት

በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከስነ ምግባር ጉድለት እና ከእምነት ጋር በተያያዘ ለረዥም ጊዜ ከባለስልጣናት ጋር ሲታገል ኖሯል፡፡ ከመንግስት ጋር መሞዳመድ የሚባል ነገርንም አያውቅም፡፡ በተለይ በቁስጥንጥንያ እያለ አብዝቶ ስለነዚህ ባላስልጣናት ያስተምር ነበር፡፡ በሱ እይታ መንግስት (ባለስልጣንነት) የሚያሳየው እኩል ያለ መሆንን፣ መበላለጥ ወይም እልቅና መኖሩን ነው፡፡ የተመሰረተውም በእግዚአብሔር ሲሆን (የሳዖልን ለመግለጽ ነው) መክንያቱ ግን ሐጢአት ነው ብሎ ይለናል፡፡ ይህንምም ሲገልጽ ‹‹ሰዎች ሁሉ በገነት በመንግስተ ሰማያት እኩል ስለሆኑ፣ በዛ መበላለጥ ስለሌለ መንግስት በዛ አያስፈልጋቸውም፡፤ ይሁን እንጂ በዚህ ሐጢአት በነገሰበት ምድር የማህበራዊ ሕይወት ደህንነት የተጠበቀ ይሆን ዘንድ የመንግስት መኖር አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው፡፡››

ያለ መንግስት ሰላምና ስርዓተ አይኖርም፡፡ ይሁን እንጂ በስልጣን ላይ ያሉ ሰዎችም ልክ እንደ ማንኛውም ሰው ሐጢአተኞች ናቸወ፡፡ በዚህም ምክንያት መንግስት እራሱ መጥፎ እና ኢፍትሐዊ ሲሆን ይታያል፡፡ ይህ ግን ለነሱ መገዛትን ወይም ስልጣናቸውን አይቀንስም፡፡ ሁሉም ሰው ለመንግስት ሕግ መገዛት ይኖርበታል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግስት በቅጽረ ቤተክርስቲያን እንዲደርስ ስለማይፈቀድ ስልጣኑ የተገደበ ነው፡፡ ቤተክርስቲያንን እንዲያገለግሉ የተጠሩ ካህናት፤ የቆሰሉ ሰዎችን ከሐዘናቸው የማጽናናትን፣ የማረጋጋትን ስራ ያደርጋሉ፡፡ ፍርድ ቤቶች ፍራቻን በሰዎች ልብ ሲዘሩ ካህናት ግን እነዚህን ሰዎች ያረጋጓቸዋል፣ መንግስት በዛቻ፣ በመሳሪያ ሲያስፈራራ ቤተክርስቲያን ግን በፍቅር ታጸናለች፡፡ ስለሆነም እግዚአብሔር በሁለቱም (በመንግስትም፣ በቤተክርስቲያንም) እንድን ዘንድ ፈቅዷል፡፡ መንግስትን አመጸኞችን ያስታግስ ዘንድ ያስታጠቀ ሲሆን ካህናትን ደግሞ ያዘኑትን ያረጋጉ ዘንድ በመንፈስ ቅዱስ እንዲሾሙ አድርጓል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በመንግስት ስልጣን ላይ ያሉትን አስተዋይ ይሆኑ ዘንድ ማስተማር ካህናት ግዴታ አለባቸው፡፡ ሲያጠፉም ሊገስጹ ሊያወግዙ ይገባል፡፡ የአንድ ካህን ስልጣን ከመጨረሻው ንጉስም የበለጠ ነው፡፡ በመሆኑም ንጉስ እንኳን የካህንን እጅ ይስም ዘንድ ዝቅ ማለት ይገባዋል፡፡ (Therefore even the emperor bows his head under the hand of the priest) በብሉይ ኪዳን ነገስታት ይሾሙ የነበረው በካህናት ተቀብተው ነበር፡፡ ካህናት ምንም እንኳን ያለ ፍርሃት በድፍረት እንዲናገሩ ቢፈቀድም ኃይልን ግን በመጠቀም እንዲያስገድዱ አይመከረም፡፡ እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የመንግስት ባለስልጣናት ሁልጊዜም ሊከበሩ ይገባል፡፡ ይሁን እንጂ ምንግዜም ከበቤተክርስቲያን አገዛዝ በታች መሆናቸውም ሊታወቅ ይገባል ይለናል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ከመናፍቃን ጋር በሚያደርገው ትግል እንኳን፤  በጉልበት እና በማስገደድ የሚደረጉ ነገሮችን አይቀበልም ነበር፡፡ ለክርስቲያኖችም በሐጢአት የወደቁትን በኃይልና በጉልበት ለመመለስ መሞከር በጥብቅ የተከለከለ ነው ብሎ ይላቸዋል፡፡ ‹‹እኛ የሞቱትን ወደ ሕይወት ለመመለስ እንጂ፤ ሞትን ወደ ሕያዋን ለማስገባት እንታገልም፡፡ ስለዚህ ይህን በምናደርግበት ወቅት ደግ እና ርህሩህ መሆን ይገባናል፡፡ እኔ  ምንፍቅናን እንጂ መናፍቃን አልዋጋም፣ እኔ በደልን መታገስ እንጂ መበደልን አልተማርኩም፣ መሰደድን መታገስ እንጂ ማሳደድን አልተማርኩም፤ ክርስቶስ ድል ያደረገው በመሰቀል እንጂ ሌሎችን በመስቀል አደለም፣ እሱ በጥፊ ተመታ እንጂ ማንንም አልመታም››

በመሆኑም ካህናት ለሥጋቸው ፍላጎት ያልተገዙ እና መንፈሳዊያን ሲሆኑ ከላይ የተገለጸውን ለማድረግ መንፈስ ቅዱስ ያግዛቸዋል፡፡ እንኳን ለባዊት ነፍስ የያዙትን ነገስታትን የዱር አውሬዎችን ሲገዙ ታይተዋልና፡፡

ይቆየን

Please follow and like us:
error0
fb-share-icon20

1 thought on “የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና የመንግስት ባለስልጣናት ግንኙነት”

  1. admin says:

    ‹ሰዎች ሁሉ በገነት በመንግስተ ሰማያት እኩል ስለሆኑ፣ በዛ መበላለጥ ስለሌለ መንግስት በዛ አያስፈልጋቸውም፡፤ ይሁን እንጂ በዚህ ሐጢአት በነገሰበት ምድር የማህበራዊ ሕይወት ደህንነት የተጠበቀ ይሆን ዘንድ የመንግስት መኖር አስፈላጊ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር ነው፡፡››

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Post

ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘኑሲስ

ሕይወቱ የቅዱስ ባስልዮስ ታናሽ ወንድም ቅ. ጎርጎሬዎስ በ335 ዓ.ም ተወለደ፡፡ የልጅነት ሕይወቱ ብዙ አይታወቅም፡፡ በቂሳርያ እቤት ውስጥ መንፈሳዊ ትምህርትን እንደተማረ ይገመታል፡፡ እሱም በአንድ ቦታ ላይ ከሐዋርያ በኋላ የተነሳ የነሱ አቻ

ዘመነ ጾም

የብልጽግናን እና የጣፋጭ ምግብን ጣዕም አትልመድ ምግብህ ቀለል ያለ እና የተመጠነ ይሁን መጽሐፍ ‹‹በሆድህ ጥጋብ አትሳሳት›› ይላልና (ምሳ 24፡15) ቴዎድሮስ ባሕታዊ ዘመነ ጾም ዘመነ ጾም የሚባለው በኢየዓርግና በኢይወርድ የተወሰነ ሆኖ

ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ የፓትሪያርኩ መልዕክት

በተዋረድ ያላችሁ ወንድሞቼ እና በጌታ የተወደዳችሁ ልጆቼ የታላላቅ ከተሞች እምብርት ከሆነችው ከተማ፣ የታላቋ ቤተክርስቲያን የሃጊያ ሶፍያ**** መገኛ ከሆነችው ከተማ፣ በዓለም ላይ ቀድሞ ባማይታወቅ መልኩ እንደ ሰው ልጆች የገጠመንን መከራ እና