+251-993-818276 akofeda@gmail.com Addis Ababa, Ethiopia

ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘኑሲስ

ሕይወቱ

የቅዱስ ባስልዮስ ታናሽ ወንድም ቅ. ጎርጎሬዎስ በ335 ዓ.ም ተወለደ፡፡ የልጅነት ሕይወቱ ብዙ አይታወቅም፡፡ በቂሳርያ እቤት ውስጥ መንፈሳዊ ትምህርትን እንደተማረ ይገመታል፡፡ እሱም በአንድ ቦታ ላይ ከሐዋርያ በኋላ የተነሳ የነሱ አቻ የሚሆን መምህሬና ወንድሜ በማለት ስለ ወንድሙ መስክሯል፡፡ ሌላ ለዛሬ ሕይወቱ እንደ ባለውለታ እና ሌላዋ መምህርቱ የሚጠራት እና የሚያሞግሳት ታላቅ እህቱ ቅድስት ማክሪና ናት፡፡

Saint Gregory of Nyssa

በወጣትነቱ በፍልስፍና ትምህርት የሚደሰት ሲሆን፣ ከክህነት በኋላ ራሱ በፍልስፍና ትምህርት ቤት ውስጥ መምህር ሆኖ ይሰራ ነበር፡፡ በዚህም መላ ቤተሰቦቹ እና በዙሪያው ያሉት በሙሉ ያዝኑበትና እና ወደ ክርስትና ሕይወቱ እንዲመለስ ይማጸኑት ነበር፡፡

ቅ.ጎርጎሬዎስ ነባቤ መለኮት በግሳጼ ‹‹ከሰዎች ሁሉ ብልህ የሆንከው ወንድሜ ሆይ ከቶ ምን ነካህ፤  በዚህ ከክፉዎች ሁሉ በካፋ እና በተዋረደ ሕይወትህ የሚያመሰግንህ የለም፡፡ በአንድ ወቅት ለሰዎች ታነብላቸው የነበረውን ጣፋጭ መጽሐፍ ትተህ ለመጠጥ የሚያሰቸግረውን ለመምረጥ ምነው በራስህ ተስፋ ቆረጥክ? ክርስቲያን ከመባል ይልቅ ፈላስፋ (ንግግር አዋቂ) መባልን ለምን መረጥክ?›› በማለት ወደ ልቡ እና ወደ ክርስትና ሕይወቱ ይመለስ ዘንድ ወቅሶታል፡፡

በዚህ በባዘነበት ወቅት ከፍልስፍናው አንጻር የአርጌንስን ሥራዎችም በብዛት ያነበበት ወቅት ነበር፡፡ የሚስጢረ ሥላሤ ትምህርቶች ላይ ያተኮሩ መልእክቶችን እየጻፈለት የአርጌንሳዊነት ተጽእኖ ውስጥ እንዳይወደቅ ወንድሙ ቅ.ባስልዮስ ብዙ ጥሯል፡፡

ቅ.ጎርጎሬዎስም የቤተሰቡን የጓደኞቹን ተግሳጽ ተቀብሎ ወደ ወንድሙ ገዳም በመግባት በመንፈሳዊ ሕይወት እና አገልግሎት መኖር ቀጠለ፡፡

ቅ. ባስልዮስ ወንድሙ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ብቁ እንዳልሆነ ብዙ ጊዜ ሲቃወመው የቆየ ሲሆን በኋላ በ371 ዓ.ም የኒሳ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አድርጎ ሾሞታል፡፡

ቅ.ጎርጎሬዎስም ከቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ይልቅ መናፍቃንን በሚቃወም ጽሑፉ ወንድሙን ሲያግዘው ቆይቷል፡፡

በ375 ዓ.ም ስለ ኦርቶዶክሳዊት እምነቱ ወደ ገላትያ እንዲሰደድ የተደረገ ሲሆን በ376 ዓ.ም የቤተክርስቲያንን ገንዘብ ያለ አግባብ ተጠቅሟል በሚል በሌለበት ተወግዟል፡፡ በግዞት 3 ዓመት ቆይቶ በ379 ወደ መንበሩ ተመልሷል፡፡ የሀገረ ስብከቱ ምዕመናን በመመለሱ በታላቅ ደስታ ቢቀበሉትመ ወዲያው ወንድሙ ቅ.ባስልዮስ እና ቅ.ማክሪና ከዚህ ዓለም በዕረፍት በመለየታቸው ታላቅ በትር አርፎበታል፡፡ ይህንንም ለኦሊምፐስ በጻፈለት ደብዳቤ ስለ እህቱ መንፈሳዊነት በጻፈው ደብዳቤ ላይ የሀዘኑ ጥልቀት ተገልጧል፡፡

በመቀጠል የወንድሙ ወራሴ መሆኑን በሚያሳይ መልኩ ቅ.ባስልዮስ ጀምሮ ያልጨረሳቸውን ሥራዎች፣ ለአውኖማዉያን ምንፍቅና 6ቅጽ ያለው መልስ የጻፈ ሲሆን ቅ.ባስልዮስ የጀመረውን አክስማሮስንም መተርጎሙ ይነገራል፡፡

ወደ ኢየሩሳሌም የሚደረግን ጉዞ ወደዛ በሚጓዙ ምዕመናን ላይ የሚደረሰውን መከራ በተሌ በሴቶች ላይ በመግለጽ ለምንድን ነው ኢየሩሳሌም የሚኬደው በማለት ተቃዉሟል፡፡ ለመንግስቱ የቀረቡ ቅዱሳን ያላደረጉትን ለምንድን ነው ምታደርጉት፡፡ ጌችታችን ወደ ኢየሩሳሌም መጓዝን እንደ አንድ መልካም ሥራ አድርጉ ብሎ አላስተማረም ኢየሩሳሌምን የጎበኙ ሰዎች ያገኙት ምን የተለየ ትርፍ አገኙ፡፡ ክርስቶስ ከእኛ በሌላ ሀገር ከምንኖር ርቆ አሁን ድረስ በሥጋ እዛ የሚኖር አደለም፡፡ ወይም ደግሞ የእግዚአብሔር መንፈስ ወደኛ ማይደርስ እና በኢየሩሳሌም ብቻ የበዛ ሆኖ አደለም፡፡ የቦታ መቀየር እግዚአብሔርን የበለጠ ወደ እናንተ አያቀርብም፡፡ መንፈሳችሁ ምቹ ከሆነ የትም ቦታ ብትሆኑ  ከእናንተ ጋር ይሆናል፡፡ ነገር ግን ውስጣዊ ማንነታችሁ አታላይ ከሆነ በጎልጎታ ብትቆሙ፣ በደብረ ዘይት ብትሆኑ፣ በትንሣኤው ቦታ ላይ ብትሆኑ ገና እንዳላመነ እና ንሠሓ እንዳልገባ ሰው ያህል ክርስቶስን ለመቀበል ሩቅ ናችሁ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ እውነተኛ ቤተልሔም፣ ጎልጎታ ወይም ደብረዘይት እግዚአብሔርን ከያዘ ልብ ውስጥ ይገኛሉ፡፡

በኢየሩሳሌም ምን አዲስ ነገር እናገኛለን፡፡ እዛ የተገለጸው ክርስቶስ እውነተኛ እንደሆነ ወደ ኢየሩሳሌም ከማቅናታችን በፊት አውቀናል፡፡ እዛ በመሔዳችን እምነታችን አልቀነሰም አልጨመረም፡፡ ቤተልሔም ከመሔዳችን በፊትም ከድንግል ሰው መሆኑን አውቀናል፡፡ ስለ ሙታን ትንሳኤም ወደ መቃብሩ ሳንሔድ በፊት አምነናል፡፡ ወደ ደብረ ዘይት ሳንወጣም በፊት የጌታን እርገት መስክረናል፡፡ አስፈላጊው ነገር ከሥጋ ወደ መንፈስ መጓዝ እንጂ ከቀጰዶቂያ ወደ ፍልስጤም መጓዝ አደለም፡፡

ቅ.ጎርጎሬዎስ በ381ኡ የቁስጥንጥንያ ጉባኤ ላይ የተሳተፈ ሲሆን በዚህ ወቅት እውቅ እና ተጽእኖ ፈጣሪ ሰውም ነበር፡፡

በ382 እና በ383 በቁስጥንጥንያ በመገኘት ከአርዮሳውያን ጋር የሚደረገውን ውዝግብ ሲመራ ቆይቷል፡፡

በቅ.ዮሐንስ የተመሰገነችውን ኦሊምፒያንም ያውቃት እንደነበር በሥራዎቹ ውስጥ ተገልጧል፡፡

በ394 በአረቢያ ባለች ቤተክርስቲያን ውስጥ የነበረውን ችግር ለመፍታት ተሳትፏል፡፡ ያረፈውም በዚህ ዓመት ወይም በ395 እንደሆነ ይገመታል፡፡ ከዚህ ዓመት በኋላ  ስለሱ ምንም የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ቅ.ዮሐንስ በነበረበት ዘመን ከሕዝብ እይታ ጠፍቶ ነበር፡፡ ከሞተ በኋላም ተጽእኖው ከፍተኛ እንደነበር የሚያሳዩ ቁርጥራጭ ጽሁፎች ተገኝተዋል፡፡

በእርሱ ዘመን የነበሩ አባቶች አርዮሳውያንን እና አፖሊናርዮሳውያንን የተቃወመ ታላቅ የኦርቶዶክስ ጠበቃ በማለት የኦርቶዶክስ ማዕዘን የአበው ሁሉ አባት በማለት ይጠራ ነበር፡፡ በኋላ በአርጌናዊነት እስከ ተጠረጠረበት ጊዜ እና ከአበው ቁጥር እንዲጠፋ እስከሆነበት ድረስ፡፡ በኋላ በኬልቄዶናውያን 7ኛ ጉባኤ መልሶ የአበው ሁሉ አባት በማለት እንዲጠራ ተደርጓል፡፡

ሥራዎች

ቅ.ጎርጎሬዎስ በሁሉም የነገረ መለኮት ጉዳዮች ላይ የጻፈ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ

የትርጓሜ ሥራዎች

ነገረ መለኮት አስመልክቶ ያደረጋቸው የጥብቅና ጽሁፎች

ከቅ.ባስልዮስ ሞት በኋላ የጻፋ ሰውን ስለመፍጠር (On the Making of Man) የሚል አክስማሮስን የብራራበት የጥብቅና ሥራ

እግዚአብሔርን ማወቂያው መንገድ ጥብቅ የሆነ መንፈሳዊነት (ascetic life) እንደሆነ የገለጸበት

  • የሙሴ ሕይወት የሚል ሥራ
  • መሀልየ መሀልይ ትርጓሜ ስራ (በዚህ ስራ መግቢያ ላይ የአሊጎሪካል ትርጓሜን አስፈላጊነት መታሰቢያነቱን ለኦሎሚፒያ በሚል ጽፏል) እናም ይህ መጽሐፍ የቤተክርስቲያን እና የነፍስ ከክርስቶስ ጋር ያላቸው ጋብቻ ብሎ ተርጉሞታል፡፡
  • በመዝሙረ ዳዊት ትርጓሜው ላይም ወደ ግብረ ገባዊ ፍጽምና ሚደረስባቸው ደረጃዎች በሚል የጻፈ ሲሆን
  • በምሳሌ ላይም ትርጓሜ ጽፏል፡፡ አብዛኞቹ ትርጓሜዎቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሲሆኑ ከአዲስ ኪዳን የተራራው ስብከት ላይ እና አቡነ ዘበሰማያት የሚለው ጌታ ያስተማረው ጸሎት ላይ ነው ትርጓሜ የሰራው፡፡

የጥብቅና ሥራዎች

ሌላው የቅዱስ ጎርጎሬዎስ የጥብቅና ሥራ በ380 እና 381 አከባቢ የተጻፉ 12 የሚሆኑ በአውኖሚየስ (አዲስ አርዮሳዊ) ትምህርት ላይ የተሰጡ መልሶች፤ ከወንደሙ ባስልዮስ የቀጠሉ፡፡ የቅ.ባስልዮስን ሚስጢራ ሥላሤ ትምህርት የሚያብራሩ ናቸው፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ለ አብላቢየስ በላከው መልእክት በሐሰት 3 አማልክትን ያመልካሉ ስለሚሉን (There Are Not Three Gods) ብሎ የጻፈው ጽሑፍም በዚሁ በቅ.ባስልዮስ የሚስጢረ ሥላሤ ትምህርት ላይ ያተኮረ ነው፡፡

በሕይወቱ ፍጻሜ አከባቢ በኦፖሊናርዮሳውያን የክርስቶስ ስጋ ሰማያዊነት እና መለኮቱ ለሰውነቱ ነፍሱ ነች የሚለውን በዝርዝር የመለሰበት እንዲሁም ለእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ለቅ.ቴዎፍሎስ በዚህ ጉዳይ የጻፋቸው መልእክቶች ከስራዎቹ የተወሰኑት ውስጥ ሚካተቱ ናቸው

እንዲሁም በመቅዶንዮስ ምንፍቅና (መንፈስ ቅዱስ ህጹጽ) እና በአርዮስ እና በሰባልዮስ ምንፍቅና ላይም ስብከቶችን ሰብኳል፡፡

ዶግማዊ ሥራዎች

ቅ.ጎርጎሬዎስ ከመጽሐፍ ቅዱስ እና ከራሱ መገለጥ ተነስቶ ኦርቶዶክሳዊ ሃይማኖትን፣ ስለ ሚስጢረ ሥላሤ፣ ስለ ሚስጢረ ሥጋዌ፣ ስለ አርነት፣ ስለ ሚስጢራተ ቤተክርስቲያን (ጥምቀት፣ ቁርባን፣ የመጨረሻ ፍርድ) በስፋት ጽፏል፡፡

ሌሎች ዶግማዊ ሥራዎቹ ለኤውስታተስ (Eustathius) የጻፈው በእንተ መንፈስ ቅዱስ እና ለ ሲምፕሊቀስ (Simplicius) የጻፈው ስለ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊነት የጻፈው የእምነት መልእክት

ስለ ነፍስ እና ስለ ትንሣኤ፣ ስለ ህጻናት ሞት እና ስለ እጣ ፈንታ የጻፋቸው ሥራዎቹ ይጠቀሳሉ፡፡

ስለ ስነ ምግባር እና ትዕርምት ሥራዎች

እንዲሁም ስለ ድንግልና(ፍጽምና)፣ አንድ ክርስቲያን ሊኖረው የሚገባው ክርስቲያናዊ ሕይወት የሚል ለኦሊምፐስ የጻፈው፣ ከ እረፍቷ በኋላ ስለ ቅድስት ማክሪና የጻፈው ስራዎቹ የትዕርምት (ascetic and moral works) ውስጥ ከሚጠቀሱ ናቸው፡፡

ስብከቶች

ስብከቶች የክርስቶስ ታላላቅ በዓላት ላይ (ገና፣ ጥምቀት፣ ትንሣኤ እና ጰራቅሊጦስ) እንዲሁም በቅ. እስጢኖስ ሰማዕቱ ቴዎድሮስ፣ የሰባስቴ አርባው ሰማዕታት፣  ስለ ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ፣ ስለ ገባሬ መንክራት ጎርጎሬዎስ እንዲሁም

የመቃብር ላይ ስብከቶች ስለ ቅዱስ ባስልዮስ፣ ስለ አንጾኪያው ሜሊጢየስ፣ ስለ ቅ.ጎርጎሬዎስ ነባቤ መለኮት የጻፋቸው ይጠቀሳሉ፡፡

ደብዳቤዎች

ከ26 እስከ 30 ሚደርሱ ደብዳቤዎችን ጽፏል፡፡

ከፍተኛ ዝንባሌው በሚታይበት በመንፈሳዊ ትዕርምት ላይ የጻፋቸው ስራዎቹ ምስጉን ስራዎች ናቸው

ዓለም ዐቀፍ የፍጥረት በዓል የሚለው የፋሲካ መልእክቱ የሰው ልጅ በሐጢያት ምክንያት ከወደቀበት መነሳቱ የሚገለትበጽ የሰው ትንሣኤ የተገለጸበት ንወ፡፡

Please follow and like us:
error0
fb-share-icon20

1 thought on “ቅዱስ ጎርጎሬዎስ ዘኑሲስ”

  1. Muluwork says:

    Very interesting. Thank you for sharing us this kind of soul’s meal. Keep it up.

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Related Post

ሲዖልን መሸጋገሪያ

ሁሉን ከምትሰለቅጠው ሲዖል በመስቀሉ ሰውን ወደ ሕይወት ያወጣው የጥበበኛው አናጺ ልጅ እነሆ፡፡ በዛፍ ምክንያት ወደ ሲዖል የወረደው የሰው ልጅ በዛፍ ምክንያት ወደ ሕይወት ተሻገረ፡፡ ከፍጥረቱ ጋር ተቃርኖ እንደሌለው እናውቅ ዘንድ

ኮሮና ቫይረስን አስመልክቶ የፓትሪያርኩ መልዕክት

በተዋረድ ያላችሁ ወንድሞቼ እና በጌታ የተወደዳችሁ ልጆቼ የታላላቅ ከተሞች እምብርት ከሆነችው ከተማ፣ የታላቋ ቤተክርስቲያን የሃጊያ ሶፍያ**** መገኛ ከሆነችው ከተማ፣ በዓለም ላይ ቀድሞ ባማይታወቅ መልኩ እንደ ሰው ልጆች የገጠመንን መከራ እና

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ

የ፳፻፲፭ ዐቢይ ጾምን ምክንያት በማድረግ ያስተላለፉት መልእክት! • በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ምእመናት እንዲሁም ኢትዮጵውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ! እንደ ስሑትና ደካማ ሰብአዊ ባሕርያችን ሳይሆን